Fana: At a Speed of Life!

ለሁለት ቀናት የተካሄደው የቡና ምርምርና ልማት ሲምፖዚየም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የነበረው የቡና ምርምርና ልማት ሲምፖዚየም የመስክ ምልከታ በማከናወን ተጠናቀቀ።

በሲምፖዚየሙ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በቡና ምርታማነት ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ የሚመለከትና ሌሎች ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ በቡና ምርታማነት ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ምርምሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው፥ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸው የምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈቱ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ ቡና ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንጻር ባለ ድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በቢኒያም ሲሳይ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.