Fana: At a Speed of Life!

ለሃገር ባለውለታ አንጋፋ አትሌቶች የገንዘብ ማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ መቶ አንጋፋ አትሌቶች ስጦታ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አበረከተላቸው።

ለእያንዳንዳቸው አንጋፋ አትሌቶች የሶስት ሺህ ብር የገንዘብ ስጦታውን የአንጋፋ አትሌቶች ፕሬዚዳንት ኮማንደር ጌጤ ዋሚ አማካኝነት ተበርክቷል፡፡

ስጦታው በየተወሰነ ጊዜ ቀጣይነት እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን እንዲህ አይነት በጎ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ስራዎች እንደ ባህል ሆነው በሁሉም ቦታ መቀጠል እንዳለባቸው ፕሬዚዳንቷ ተናግራለች።

የአንጋፋ አትሌቶች ማህበር የአፍሪካ ብሎም የዓለም አቀፍ ማህበር በፈረንጆቹ 2020 አባል ሲሆን ወደፊት በርካታ ስራዎች እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ድጋፉ በቀጣይም በቋሚነት እንዲቀጥል እተየሰራ መሆኑም ነው በዚህ ወቅት የተገለጸው።

ከስጦታው ውስጥ ግማሹ በኮሮና ወቅት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠይቆ የተገኘ ሲሆን ግማሹ ደግሞ ከአቶ አብነት ገብረመስቀል የተበረከተ መሆኑን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.