Fana: At a Speed of Life!

ለህወሓት ሊደርስ ነበር የተባለ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቆቦ ከተማ ለአሸባሪው ህወሓት ሊደርስ እንደነበር የተጠረጠረ 3 ሚሊየን ብር በቆቦ ከተማ ህዝብ እና በከተማው ፓሊስ እና ሕዝባዊ ሚሊሻ ሰራዊት አማካይነት በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ገንዘቡን ደብቆ ለማሸጋገር የተጠቀሙበት መንገድ ያልተጠበቀ ቢሆንም፥ የቆቦ ከተማ ህዝብ እና የፀጥታ ሀይሉ የተቀናጀ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ፅ ህፈት ቤት አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ገንዘቡ እንዲያዝ ለተጫወተው ሚናም ፖሊስ ምስጋናውን ማቅረቡን ከከተማዋ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.