Fana: At a Speed of Life!

ለህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሠራ የበኩላችንን እንወጣለን – ከተፎካካሪ የፖሊቲካ ፖርቲ የተወከሉ የም/ቤት አባላት

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የሚመሠረተው መንግስት ለህዝብ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ቅድሚያ ሰቶ እንዲሠራ በማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ከተፎካካሪ ፖሊቲካ ፖርቲዎች የተወከሉ የደቡብ ክልል ም/ቤት አባላት ተናገሩ።

የአማሮ ልዪ ወረዳ የኢዜማ ተወካይ አቶ ማቴዎስ ዘርፉ፥ አዲሱ መንግስት ህዝባችን ለሚያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በምክር ቤት ቆይታችን አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል።

በተመሳሳይ ከአማሮ ወረዳ የተወከሉት ወ/ሮ ታደለች ታሪኩ ወደ ምክር ቤት የመጣነው ህዝብና መንግስት መሀል ድልድይ ሆነን ለማገልገል ስለሆነ መንግስት ማየት ያልቻለውን የህዝብ ችግር በማሳየት ሀላፊነታችንን እንወጣለን ብለዋል።

የተፎካካሪ ፓርቲ አባላቱ እንዲህ አይነት የተፎካካሪ ፖርቲዎችን ያከተተ የመንግስት ስርዓት በልዩነት ውስጥ ለህዝብና ሀገር በጋራ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ከመሆኑም በላይ እኔ ብቻ ከሚል ፖሊቲካ ለመውጣት መንገድ መጀመራችንን ያሳያል ብለዋል።

በጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.