Fana: At a Speed of Life!

ለህግ ምሁራንና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በፌዴራል የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅ 1183/2013 በማርቀቅ ሂደትና ዝግጅት ላይ ለተሳተፉ የህግ ምሁራንና ባለሙያዎች እውቅና ተሰጠ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሁሉም የአስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅ፤ ተቋማት መንግስታዊ አሰራራቸውን ለህዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ እንዲሰሩ ለማድረግ፣ ሃላፊነታቸውን ያልተወጡ አካላትን ለመጠየቅ፣ በተቋማቱ አሰራርና ውሳኔ ቅር የተሰኘ ግለሰብ የመመሪያዎቹን ህጋዊነት በማስመርመር ፍትህን ለማስፈን የወጣ ነው።

አዋጁ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውና አስተዳደራዊ ፍትህ ለማስፈን የሚያስችል በመሆኑ በሰነድ ማርቀቅና ዝግጅት ለተሳተፉ አካላት ዕውቅና መዘጋጀቱን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ተስፋዬ ዳባ እንዳሉት፥ በኢትዮጵያ የህግ ስርዓቱን ለማጎልበት የተለያዩ አዋጆች እንዲወጡና እንዲሻሻሉ እየተደረገ ነው።

ከእነዚህ አዋጆች መካከል የፌዴራል አስተዳደር ሥነ ስርዓት አዋጅ 1183/2012 አንዱና አስፈላጊው መሆኑን ገልጸዋል።

“በዚህ አዋጅ በጥናት ላይ የተመሰረተ ዝግጅት ላይ የተሳተፉ የህግ ምሁራንና ባለሙያዎች ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል።

የሚወጡ ህጎች በአግባቡ ተግባራዊ መደረግ እንዳለባቸው ጠቅሰው፥ ለገቢራዊነቱ ሁሉም አካል በትብብር መስራት እንዳለበትም ነው ያሳሰቡት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.