Fana: At a Speed of Life!

ለ’ሆቴል ሩዋንዳ’ ፊልም መነሻ የሆነው ግለሰብ በሽብር ክስ ጥፋተኛ ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆቴል ሩዋንዳ’ በተባለው ዝነኛ ፊልም ላይ የሕይወት ታሪኩ ታይቶ እውቅናን ያተረፈው ፖል ሩሴሳቢጊና ከሽብር ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባለ።

በሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ላይ በሚያጠነጥነው ‘ሆቴል ሩዋንዳ’ ፊልም ላይ የጀግና ሚና ተላብሶ ታሪኩ የተነገረለት ፖል ካለፈው የካቲት ጀምሮ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነበር።

የሩዋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ  ባሳለፈው ውሳኔ መሠረትም ፖል ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት የተባለ ሕገወጥ የታጣቂ ቡድን ካቋቋሙ አንዱ በመሆኑ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህንን ቡድን በገንዘብ ይደግፍ እንደነበርም ፍርድ ቤቱ አመልክቷል።

ይህን ተከትሎም ፖል በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ዐቃቤ ሕግ ጠይቋል።

 

ምንጭ ፡- ሮይተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.