Fana: At a Speed of Life!

ለመተከል ዞን ፀጥታ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመፈለግ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመተከል ዞን ፀጥታ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመፈለግና ለማረጋጋት በዞኑ ከሁሉም ወረዳ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የህዝብ ለህዝብ የሰላም ኮንፈረንስ በግልገል በለስ ከተማ ተካሄደ፡፡
 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በዞኑ ከሁሉም ወረዳ ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎችን ተወያይተዋል።
 
ውይይቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ለረጅም ጊዜያት ለዘለቀው የጸጥታ ችግር ዘላቂ መፍትሔ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።
 
በዞኑ አንፃራዊ ሰላም ለማስፈን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀምሮ በየደረጃው ያለው የፀጥታ አካላት ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አብርክተዋል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.