Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ ከህዝቡ ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአገር መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና ከ971 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነት ድጋፍ በህዝቡ መደረጉን የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ የኀብረተሰቡን ድጋፍ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ አንድ በመሆን ለሰራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት በተግባር አሳይተዋል ብለዋል።
የህልውና ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ እስካሁን ድረስ ለሰራዊቱ 971 ሚሊየን 500 ሺህ ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ በህዝቡ መደረጉን ተናግረዋል።
 
ይህም ኢትዮጵያዊያን ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት በተግባር ያረጋገጠ ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
 
በተጨማሪም ለሰራዊቱ ገቢ ማሰባሰቢያ በተከፈተው የባንክ አካውንት ከ2 ቢሊየን 41 ሚለየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ነው የገለጹት፡፡
 
በ6800 አጭር የጽሁፍ መልዕክት የገቢ ማሰባሰቢያም ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
 
በዚህም ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ነው የተናገሩት።
 
የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰራዊቱ በተግባር እያሳየ ያለውን ደጀንነት አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.