Fana: At a Speed of Life!

ለመጀመሪያ ዙር የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ዙር የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኞች ተመድበውባቸው በሄዱባቸው ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በቪዲዮ ኮንፈረንስ የህይወት ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ስልጠናው ሰልጣኞቸ በራስ መተማመን ችሎታቸውን በማሳደግ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ቶሎ እጅ ባለመስጠት ችግሩን ተቋቁመው ለማለፍ እንዲችሉ፣ ጊዜን በአግባቡ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በህይወት ተሞክሯቸው ያላቸውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለመለየት የሚያስችላቸው ስልጠና መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.