Fana: At a Speed of Life!

ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው የወባ ክትባት ከመቶ አመት በላይ የተደረገ ጥረት ውጤት ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ማእከል (ሲዲሲ) ዳይሬክተር ጆን ኔኪንጋሶንግ ለመጀመሪያ ግዜ የተገኘው የወባ ክትባት ለህክምናው ዘርፍ ትልቅ እመርታ መሆኑን ተናገሩ፡፡
ወባ በአፍሪካ ታዳጊዎችን በመግደል ቀዳሚው መሆኑን ጠቁመው÷ ክትባቱ የልጆች ሞትን በመቀነስ የራሱ ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ወባ በአፍሪካ በአብዛኛው ህፃናትን እንደመግደሉ፣ የክትባቱ ውጤታማነት አስከፊ ህመምንና ሞትን በመከላከሉ ረገድ ትልቅ እመርታ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ ክትባቱ ከመቶ አመት በላይ የተደረገ ጥረት ውጤት ነው ብለዋል፡፡
ወባ በሽታ የመከላከል አቅምን በማጥቃት ባህሪው አደገኛና አስቸጋሪ ጥገኛ ተሃዋሲያን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ክትባቱን በክሊኒካል ሙከራ እውን እንዲሆን ላስቻሉም የአፍሪካ ሀገራት ማላዊ፣ ኬኒያ እና ጋና ምስጋና አቅርበዋል ዳይሬክተሩ፡፡
በአፍሪካ አመራርና በእንችላለን መንፈስ “ለራሳችን የጤና ችግር መፍትሄ ሰጥተናል” ብለዋል፡፡
በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ የአለም ጤና ድርጅት ለክተባቱ እውቅና መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ድርጅቱ ክትባቱ ለ30 አመታት በእንግሊዙ ፋርማሲቱካል ካምፓኒ ግላክሶ ስሚዝ ክላይን ከሌሎች አጋሮችና በአፍሪካ ካሉ የምርምር ማእከላት ጋር መሰራቱን አሳውቋል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠው እኤአ ከ2019 ጀምሮ 2.3 ሚሊየን ዶዝ ክትባት በጋና፣ኬኒያ እና ማላዊ በ 800 ሺህ ህፃናት ላይ ተሞክሮ ውጤት በማሳየቱ እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.