Fana: At a Speed of Life!

ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም – ጠ/ሚ ዐቢይ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም ሲሉ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የጁምዓ ዕለት የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ነፍሱን በይቅር ባይነት አንጽቶ፣ ልብሱንም በመልካም መዓዛዎች አጥርቶ በፈጣሪው ቤት የሚሰባሰብበት የተወደደ ዕለት” መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

አያይዘውም ሙስሊም ወገኖች “ይህ ዕለት ለሀገራችን ሰላም የምትጸልዩበት እንዲሁም ለትውልድ የሚተርፍ መልካም አሻራችሁን የምታሳርፉበት” ይሁን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“ለመጪው ትውልድ የምናስረክባት ኢትዮጵያ ሁሉም በሰላም የሚኖርባትና ለምለም ምድር ለማድረግ አብረን እንቁም” ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “ዐሻራችን ለትውልዳችን” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.