Fana: At a Speed of Life!

ለሚያንኮራፉ ሰዎች መፍትሄ ይሆናል የተባለው አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)ለሚያንኮራፉ ሰዎች መፍትሄ ይሆናል የተባለው አዲሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ  ይፋ ተደርጓል።

ሚሊዮኖች የሚሰቃዩበት ማንኮራፋት ከጤና መቃወስ ጋር በተያያዘ በቂ የሆነ እንቅልፍ ከመከልከሉ በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኙትን ሰዎች በመረበሽ ማህበራዊ ኑሯችንን ያውካል፡፡

መንስኤዎቹ የመተንፈሻ አካላት የተፈጥሮ ሁኔታና ህመም ሲሆኑ ከ60 እሰከ 80 በመቶ ከ50 አመት በላይ በሆኑ ወንዶች ላይ አንደሚከሰት ጥናቱ ያመላክታል፡፡

አዲሱ ፈጠራም  የመተንፈሻ አካላትን የአተነፋፈስ ስረዓት በማሻሻል እና በማገዝ ማንኮራፋትን የሚያስወግድ ነው ተብሏል፡፡

ቴክኖሎጂው በአፍንጫ የሚቀመጥ ሲሆን ነርቮችን በማነቃቃት የአተነፋፈስ ስርዓትን በማስተካከል አየር በአግባቡ እንዲዘዋወርና ማንኮራፋትን በማስወገድ ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ያስችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፣ ecoplanetdeals.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.