Fana: At a Speed of Life!

ለሠራዊት አባላት ቤተሠቦች የምንሰጠው ክብርና እንክብካቤ ለሙያው ያለንን ፍቅር ይጨምራል- ዋና ኢንስፔክተር ሀሰን ሙሀመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሠራዊት አባላት ቤተሠቦች የምንሰጠው ክብርና እንክብካቤ ለሙያው ያላቸዉን ፍቅር እንደሚጨምር የደሴ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሀሰን ሙሀመድ ገለጹ፡፡

እናቶች ልጆቻቸውን ሴቶች ባለቤታቸውን መርቀው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለልዩ ሀይል አባልነት ሲሸኙ እኛ እነርሱን ማክበርና መደገፍ ይገባናል ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ÷ ይህንን ስናደርግ ለሙያው ፍቅርን እንገነባለን ብለዋል፡፡

በደሴ ከተማ አስተዳደር የዘማች ቤተሠቦች የመከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ልዩ ሀይል ቤተሠቦች ነጻ የትምህርት እድል እንዲሠጣቸው መወሰኑንም ተናግረዋል፡፡

እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ ገምግመናል ያሉት ዋና ኢንስፔክተር ሀሠን÷ እንደኢኮኖሚያዊ ሁኔታቸው አንድ ቤት ለአንድ ወገን ፕሮግራም ተሣታፊ እንዲሆኑ ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ተነጋግረናልም ነዉ ያሉት፡፡

የቀድሞ የደሴ ከተማ ልብስ ሠፊወች ማህበር በአራዳ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ለመከላከያ እና ለአማራ ልዩ ሀይል ለዘማች ቤተሠቦች 110 ሺህ ብር የሚገመት 25 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ይህ አይነቱ ለዘማች ቤተሠብ የሚደረግ ድጋፍ ከተማችን በቂ ወጣቶችን ወደ መከላከያ ሰራዊትና ወደ ልዩ ሀይል አባልነት እንዲሳተፉ ተነሳሽነትን እንደሚጨምር ነዉ የገለጹት፡፡

በቀጣይም በከተማ አስተዳደር ደረጃ በዘላቂነት በታቀደ መልኩ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.