Fana: At a Speed of Life!

ለሰራዊቱ የሚደረገው የስንቅ ዝግጅት ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል-የጌዲኦ ዞን እናቶች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ስንቅ ዝግጅት ተጠናክሮ መቀጠሉን በጌዴኦ ዞን የሚገኙ እናቶች ገለፁ፡፡
 
የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የመንግሥት ረዳት ተጠሪና የገቢ አሰባሰብ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ለምለም ከበደ አሸባሪው ህወሓት እየፈፀመው ያለውን የሽብር ድርጊት ለመመከት በህልውና ዘመቻ ላይ ለሚገኙ ለመከላከያ ሠራዊት ለ5ኛ ዙር የስንቅ ዝግጅት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡
 
በዚህ ዙር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ሃብት ለማሰባሰብ መታቀዱን ነው ወ/ሮ ለምለም የገለጹት፡፡
 
የስንቅ ዝግጅቱ ሥራው ተሳታፊ እናቶች በበኩላቸው÷ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር የማይተካ ውድ ህይወቱን በመክፈል ላይ መሆኑን በመጠቆም ከስንቅ ዝግጀት ጀምሮ በሚያሰፈልገዉ ሁሉ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጎን እንሆናለን ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.