Fana: At a Speed of Life!

ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ስንዴ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ስንዴ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በዛሬው እለትም ከ12 ሺህ ኩንታል በላይ ስንዴ የጫኑ 30 ተሽከርካሪዎች መቐለ ከተማ መግባታቸውንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው።

በአዳማ እና ኮምቦልቻ ከሚገኙ መጋዘኖች የተጫነው ስንዴ በዕለት ደራሽ እርዳታ ትራንሸዠስፖርት በኩል ነው እየጓጓዘ ያለው።

በቀጣይም ተጨማሪ የሰብአዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ እየተሰራ ነው መሆኑንም አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በትናንትናው እለት ወደ ሽሬ ከተማ በ44 ከባድ የጭነት መኪና የተላከው ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች መድረሳቸውንም ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

በአሁኑ ሰአትም እርዳታውን ለማከፋፈል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ይገኛል።

በተመሳሳይ ባለፉት አምስት ቀናት ወደ አላማጣ ከተማ የተላከው የእለት ደራሽ እርዳታ በመከፋፈል ላይ መሆኑን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

በተጨማሪም 15 ሺህ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ እህል ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የብሔራዊ የአደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት እየተደረገ ያለው ድጋፍ በመንግስት ብቻ መሆኑን ጠቁመው፤ እርዳታው ሩዝ፣ ዱቄትና ሌሎች ምግብ ነክና ተያያዥ ቁሳቁሶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በፋሲካው ታደሰ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.