Fana: At a Speed of Life!

ለስኳር ታማሚዎች ቆሽትን ተክቶ የሚሰራ ቴክኖሎጂ ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የዓይነት 1 የስኳር በሽታን መቆጣጠር የሚያስችል ሰው ሰራሽ የቴክኖሎጂ ሙከራ ላይ አስደናቂ ውጤት መገኘቱ ተሰማ፡፡

ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው ይህ መሳሪያ በሰውነት ቆዳ ውስጥ በሚቀበሩ ሴንሰሮች አማካኝነት ቆሽታቸው ኢንሱሊን ማምረት ያቆመ የስኳር ታማሚዎችን (የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ተጠቂዎችን) የስኳር መጠን ባለማቋረጥ የሚከታተል ይሆናል ነው የተባለው፡፡

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በቆሽት አማካኝነት አስፈላጊው የኢንሱሊን መጠን በደም ስሮች እንዲሰራጭ ትዕዛዝ ይሰጣል ተብሏል፡፡

መሳሪያውን ታማሚዎቹ የደም ስኳር መጠናቸውን ለመለካት፣ለመቆጣጠር የሚወስዱትን ጊዜ ፣በአጋጣሚ የስኳር መጠናቸው ዝቅ ብሎ ለሕይወታቸው አስጊ ሆኖ ቢገኝ ወደ ሕክምና እንኪደርሱ የሚደረሰውን ጉዳት ያስቀራልም ነው የተባለው፡፡

እስካሁን ድረስም የዓይነት 1 የስኳር ሕመም ያለባቸው 1ሺህ ሰዎች ተለይተው የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂው እየተገጠመላቸው መሆኑን ዴይሊ ሜይል አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.