Fana: At a Speed of Life!

ለሽብር ድርጊት ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሽብር ድርጊት ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች በአፋር ክልል በጋላፊ ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ መያዛቸውን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
 
አሸባሪው ቡድን ለጥፋት ተግባሩ ማስፈፀሚያ ለማዋል አስቦ ያዘጋጃቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች፣ የጦር ሜዳ መነፅሮች፣ የፀጥታ አካላት የደንብ ልብሶች፣ የተጠቀለሉ ፈንጂዎች፣ ሐሰተኛና ህገ-ወጥ ሰነዶች፣ በርካታ ገንዘብ ያላቸው የባንክ ደብተሮች እንዲሁም ከ200 ሺህ ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ በጋላፊ ከተማ በተደረገው የቤተ ለቤት ፍተሻ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር ሊያውል ችሏል።
 
በተመሳሳይም፣ በአፋር ክልል ጋላፊ ከተማ የሚገኙ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለሽብር ድርጊት ሊውሉ የነበሩ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ ሀገራችን በሁሉም መስክ ህልውናዋ እንደጠላት መሻት ሳይሆን እንደሀገር ወዳድ ዜጎቿ ፍላጎት ሳይደፈር ወደፊት እንዲቀጥል የሚጠበቅባቸውን መስዋዕትነት እየከፈሉ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በከፍተኛ ተነሳሽነት እየተወጡ ይገኛሉ።
 
የሀገራችን የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን የኢትዮ-ጅቡቲ ዋና መንገድ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከአፋር ህዝብ ጋር በመቀናጀት የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
 
የሠራዊቱ አባላት የአሸባሪውን ህወሓት ሀገር የማፍረስ ዓላማ በመመከት በአፋር ክልል ለሚያልፈው ዋና መንገድ አስተማማኝ ጥበቃ በማድረግ ላይ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
 
ለቀጠናው ሰላም በዘላቂነት በህዝብ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ ተነሳሽነት ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር እየተወጡ እንደሚገኙም ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.