Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ መሳካት የምርጫ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ችሎቶች መዘጋጀት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቀጣዩ ሃገር አቀፍ ምርጫ መሳካት የምርጫ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ችሎቶች መዘጋጀት የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለጸ።
የምርጫ ጉዳዮችን ከሚመለከቱ ችሎቶች የሚጠበቀውን ሚና እና ሃላፊነትን የተመለከተ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ውይይቱን ያዘጋጁት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በጋራ ነው።
በመድረኩ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ፣ የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ላይ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የምርጫ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ችሎቶች ተመስርተው በዚህ መልኩ የጋራ ውይይትና ስራዎች መጀመራቸው ለምርጫው ስኬታማነት የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተገልጿል።
በመድረኩ የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አረጋን ጨምሮ የክልል ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችና ምክትሎቻቸው እንዲሁም ዳኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.