Fana: At a Speed of Life!

“ለበርካታ ዓመታት ንፁሃን ዜጎች በጅምላ በተገደሉበት ስፍራ የት/ቤት ግንባታ በማስጀመራችን ደስታ ይሰማናል!” – አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶማሌ ከልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በቀብሪዳሀር ከተማ ለሚገነባው በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠዋል።

ትምህርት ቤቱ “ሰዎች ለሰዎች” በተባለው የጀርመን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚገነባ መሆኑም ተገልጿል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ÷ በወቅቱ የቀብሪዳሀር ከተማ እያደገች በመሆኗ የትምህርት አገልግሎትን በማጠናከር ጥራትና በቂ እውቀት ያለው ትውልድ መገንባት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ለበርካታ ዓመታት የክልሉ ንፁሃን ዜጎች በጅምላ በተጨፈጨፉበት ስፍራ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በማስጀመራቸው ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማቸውም ተናግረዋል፡፡

የቀብሪዳሀር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎችም የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም በርካታ ንፁሃን ዜጎች በጅምላ ተገድለው በተቀበሩበት ስፍራ ለመታሰቢያነት የ2ኛ ደረጃ በማስገንባቱ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.