Fana: At a Speed of Life!

ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች ታግደዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው-የአ/አ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
ቢሮው ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ ተደርጎ የሚዘዋወረው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡
 
ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ታክሲዎች በተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል፡፡
 
በቀጣይም የትራንስፖርት እጥረቱን በተመለከተ ግምገማ ተደርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚቀመጥና ዝርዝር መረጃም የሚሰጥ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ስለሆነም የተማሪዎች ሰርቪስን በሚመለከት አዲስ መመሪያ እስኪወጣ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ታክሲዎች በነበሩበት ሥራ እንዲቀጥሉ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስሴክሬተሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.