Fana: At a Speed of Life!

ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የስፖርት ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ታሳቢ ያደረገ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በወረርሽኙ ምክንያት ከገባበት ችግር እንዲወጣና እንዲነቃቃ ስፖርታዊ ኩነቶችን ማስተናገድ አስተዋፅኦ እንዳለው ታምኖ እየተሠራበት መሆኑን ኮሚሽነር ኤሊያስ ሽኩር ተናግረዋል፡፡
ዝግጅቶቹን ስኬታማ ለማድረግ በከፍተኛ ጥንቃቄ ዝግጅቱን የሚመራ ዐብይ እና ንዑስ ኮሚቴዎች እንደተቋቋሙም አስታውቀዋል፡፡

ስፖርታዊ ኩነቶቹን ከማስተናገድ ጎን ለጎን የአፍሪካ ወጣቶች ኦሎምፒክ የANOCA ጉባኤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሰጠውን ሽልማት ከግምት ውስጥ በማስገባት የሃገርን መልካም ገፅታ ለተቀረው ዓለም ለማሳየት የሚረዳ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም እንደሚሰጠውም አቶ ኤሊያስ መናገራቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.