Fana: At a Speed of Life!

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠርና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ወሳኝ ሚና አለው- አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፖሊሲው ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ ለአምራች ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳካት የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሁሉም ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ምክትል ሰብሳቢዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ የከተማ አስተዳዳር ምክትል ከንቲባዎች፣ የክልልና የከተማ አስተዳዳር የመሰረተ ልማት ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያላክታል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል በውይይቱ ላይ እንደገለጹት÷ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳካት የኢንዱስትሪ ፖሊሲው ወሳኝ ሚና አለው፡፡
የዘርፉን ዕድገት ለማፋጠን የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ መጀመሩንና ተስፋ ሰጭ ለውጦች እየታዩ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ለውጦቹን በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ለማስቻል በፖሊሲዎች፣ በሕግ ማዕቀፎች እና በመመሪያዎች ተደግፈው መሰራት እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡
ይህን ተግባራዊ ለማድረግም በዘርፉ ያሉ የሕግ ማዕቀፎችን ማሻሻል፣ ፖሊሲዎችን መከለስ እና መመሪያዎች እየተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.