Fana: At a Speed of Life!

ለአስም ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚውሉ የ150 ማሽኖች የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአስም ታማሚዎች የህክምና አገልግሎት የሚውሉ የ150 ማሽኖች የድጋፍ ስምምነት ተፈረመ።

የጤና ሚኒስቴር ከአስትራዜኒክ ሶሳይቲት ጋር ያደረገጉት ስምምነት በከፍተኛ የአስም ህመም ላይ ለሚገኙ ዜጎች ህክምናውን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያደርግና ለባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል ነው።

የፊርማ ስነስርአቱን ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ እና የአስትራዜኒክ ሶሳይቲ የአፍሪካ ዳይሬክተር ባረባራ ኔል ናቸው።

የስምምነት ፊርማው ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን መሳሪያዎቹ በሁለት ዙር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

ማሽኖቹ በ47 የጤና ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ እየተንሰራፋ የመጣውን ተላላፊ ያልሆነ በሽታ ከመከላከል በተጓዳኝ ህክምናው ላይም ሰፊ ስራ መስራት እንደሚገባ በስነስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅት ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ዛሬ ከአስትራዜኒካ ሶሳይት ጋር የተፈረመው ስምምነትም የዚሁ አካል ነው ተብሏል።

በስምምነቱ መሰረት 150 የህክምና ማሽኖች በ2 ዙር ይቀርባሉ፡፡

በኃይለየሱስ ስዩም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.