Fana: At a Speed of Life!

ለአንድ ወር የሚቆይ የኮሮና ቫይረስ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 25 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአንድ  ወር የሚቆይ የኮሮና ቫይረስ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

በዘመቻው በነሀሴ ወር የመጀመሪያው 2 ሳምንታት 200 ሺህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱ ተገልጿል።

በዚህም በኮቪድ 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር የመጀመሪያው 1 ሺህ ለመድረስ 79 ቀናትን የፈጀ ሲሆን÷ አሁን ግን በሁለት ቀናት ውስጥ 1 ሺህ ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል ።

ይህም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ስለመምጣቱ ማሳያ ነው ተብሏል።

ስለሆነም የስርጭቱን መጠን በአግባቡ ለማወቅና ለመቆጣጠር  ታልሞ ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ምርመራ ዘመቻ ይፋ መደረጉም ነው የተነገረው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት የማስክ አጠቃቀም 76 በመቶ ፣ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ 38 በመቶ ፣የእጅ ንጽህና አጠባበቅ 28 በመቶ መሆኑን አመላክቷል።

ስለሆነም የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በርካታ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አመላክቷል።

በማህበረሰብ አቀፍ ዘመቻው የሚገኘው ውጤት ለቀጣይ 2013 ዓ.ም ስራዎች መሰረት እንደሚሆንም ተገልጿል።

በዘመቻው ስኬታማነትም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል

በአላዛር ታደለ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.