Fana: At a Speed of Life!

ለአካባቢ ጥበቃ እየተሰራ ያለ ሥራና የወላይታ ሶዶ ህዝብ ተሳትፎ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ ለተውጣጡ በአካባቢ ጥበቃና ጸጥታ ዘርፍ ሲሰጥ የነበረውን ሥልጠና አጠናቋል፡፡
 
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አክሊሉ ለማ÷ተመራቂ ሠልጣኞች የአከባቢያቸውን ሠላም ከማስጠበቅ ባለፈ ወደ ግንባር በመዝመት የሀገርን ህልውና የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።
 
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገርናቸው ተመራቂዎች በበኩላቸው÷ ሀገራችንን ለመጠበቅና ለአካባቢያችን ሠላም ዘብ ለመሆን ከመንግስት ጎን ቆመን ለሀገር ሕልውና ለመታገል ዝግጁ ነን ብለዋል።
 
የሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ መርክነህ ማለዳ ተመራቂዎች በ አንድ ብርጌድ የተደራጁ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ በመቀበል እስከ ግንባር ድርስ መዝመት የሚችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
ከተማ አስተዳደሩ ለ5ኛ ዙር ለመከላከያ ሠራዊት የተለያዩ አይነት ድጋፎችን እንዳደረገም አስታውሰዋል፡፡
 
በማህሌት ኡኩሞ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.