Fana: At a Speed of Life!

ለአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሚያጣራው የሚኒስትሮች ግብር ሀይል ዙሪያ ገለፃ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴር ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለተወጣጡ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ አጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የተመሰረተው የሚኒስትሮች ግብር ሀይልን በተመለከተ ገለፃ አደረገ።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ‘‘የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል’’ የሚለውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርትን ተከትሎ መንግስት አጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማስቻል እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግብረ ሃይል ፅህፈት ቤትን ማቋቋሙ ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች የተቋቋመው የሚኒስትሮች ግብረ ሀይል ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ተከትሎ ለግብረ ሀይሉ በፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና ፅህፈት ቤቱን በሚመሩ በዶክተር ታደሰ ካሳ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህም ግብረ ሀይሉ የተቋቋመበት አላማ፣ እቅድ እና አደረጃጀት እንዲሁም እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በዝርዝር ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

በተጨማሪም ስለሀገራዊ የምክክር መደረኩ የመንግስት ሀሳብና እይታ ለአምባሳደሮቹ እና ለዲፕሎማቶቹ ማበራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ግብረ ሃይሉ ተቋቋመ የሚለውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጋራ ሪፖርት ውጤትን መሰረት አድርጎ ቢሆንም ጥምር ቡድኑ ከመረመረው ውጪ ሰፋ አድርጎ በማየት በግጭቱ አውድ በአፋር፣ በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ያጋጠሙና የተፈፀሙ የመብት ጥሰቶችን የመመርመር እንዲሁም ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እና ተያያዥ የሆኑ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን እና ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ወገኖችን አስፈላጊ የሆነ የማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የማድረግ ዝርዝር እቅዶች ናቸው የቀረቡት፡፡

ግብረ ሀይሉ አራት የሚሆኑ ኮሚቴዎች እንዳሉትም ነው ገለፃ የተደረገላቸው ፡፡

የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች ለተደረገላቸው ማብራሪያ አመስግነው፥ መሰል ተግባራት በቀጣይም ለህዝቡና እንደ አጋርም ለህብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶች እንደሚቀጥል ተስፋቸውን ገልፀዋል።

በጸጋዬ ወንድወሰን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.