Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያዊነት እሴት መጎልበትና ህዝባዊ አንድነት የኪነ-ጥበብ ሚና የጎላ ነው- አርቲስት ተስፋዬ ሲማ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያዊነት እሴት መጎልበትና የአብሮነት ጽናት እና በስነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመገንባት የኪነ-ጥበብ ሚና የላቀ በመሆኑ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው ተስፋዬ ሲማ ተናገረ።

በህወሓት ዘመን የኪነ-ጥበብ ተቋማት እንዲዳከሙ፣ የታሪክ ትምህርት እና አገራዊ የመከባበር እሴቶች እንዲጠፉ መደረጉን የገለጸው አርቲስቱ ፥ የኪነ-ጥበቡ መውደቅ ከኢትዮጵያዊነት እሴቶች መዳከም ጋር ይያያዛል ብሏል።

የተዘጉ ቴአትር ቤቶችን መክፈት፣ የኪነ-ጥበብና ግብረገብ እሴቶችን በትምህርት ሥርዓቱ ማካተት፣ ለኪነ- ጥበብ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች መደገፍ ላይ መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ አርቲስቱ ጠይቋል።

በቅርቡ ወደ አገር ቤት የተመለሰው አርቲስት ተስፋየ ሲማ ኢትዮጵያን ለማዳን አንዱ ቁልፍ መሳሪያ ኪነ-ጥበብ እንደሆነ አብራርቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.