Fana: At a Speed of Life!

“ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም” የሚል ግብረ ኃይል በአውሮፓ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኢትዮጵያ ዘብ እንቁም “ዲፌንድ ኢትዮጵያ” የሚል በአውሮፓ አንዳንድ የፓርላማ አባላትና መንግስታት እያስተጋቡ ያሉትን የተዛቡ መረጃዎች ለመከላከል ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡

ግብረኃይሉ ከዚህ በተጨማሪም በዲፕሎማሲ እና በመወትወት (ሎቢ)፣ በማህበራዊና በዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ መረጃ ለማረምና በሎጅስቲክስ ማሰባሰብ ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡

እንዲሁም ግብረ ኃይሉ በመንግስት ላይ ያነጣጠሩ አሉታዊ ጫናዎችን በመቀነስ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን ሁለገብ የለውጥ ሂደት ለማገዝ ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ግብረ ኃይሉ ከሰባ በላይ ከፍተኛ ምሁራንና ወጣት የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎችን አሰባስቧል፡፡

በአውሮፓ ደረጃ ተጠናክሮ እና ተቀናጅቶ ቢቀጥል የፓርላማ አባላትን፣ ቲንክ ታንክ ቡድኖችን እና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ በቀላሉ መቀነስ ያስችላል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያውያኑና እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በበኩላቸው፤ የዲጂታል ዲፕሎማሲና የመወትወትና ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ ቃል ገብተው የዘመኑ መረጃ ፈጣን እና ጊዜን የማይጠይቅ በመሆኑ ሳያቋርጥ መረጃ ሊያቀብል የሚችል ማዕከል እንዲፈጠር መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.