Fana: At a Speed of Life!

ለከተማ ግብርናና ለችግኝ ተከላ መርሀግብር እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለከተማ ግብርናና ለችግኝ ተከላ መርሀግብር እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶችን በተመለከተ ውይይት ተደረጓል።

በተያዘው አመት በከተማ ደረጃ ለታቀደው 7 ሚሊየን ችግኝ የመትከል እቅድ የመሬት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የችግኝ ዝግጅቶችም እየተደረጉ ይገኛሉ።
የችግኝ ዝግጅቱ በአስተዳደሩና በተደራጁ ወጣቶች የተደረገ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የከተማ ግብርናን በተመለከተም በየክፍለ ከተማው የመሬት ዝግጅቱ ተጠናቆ ወደ እርሻ ተገብቷል ነው የተባለው።

የመሳሪያና የዘር አቅርቦቶችም እየተከAናወኑ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።

የከተማ ግብርናን በተመለከተ የተለያዩ ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦችና ባለሙያዎች በኦንላይን የተመዘገቡ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ወደ ስራ የሚገቡ ይሆናል ተብሏል።

በውይይቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ እንዲህ አይነት ፈታኝ ወቅቶችን መሻገር የምንችለው በምግብም ይሁን በተለያዩ ነገሮች ራሳችንን ስናዘጋጅ ነው ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ያቀደው የከተማ ግብርና መርሀግብርም ህብረተሰቡ በቀላል መንገድ ምርቶችን በማዘጋጀት ሊከሰቱ የሚችሉ የምግብ እጥረቶችን ከመፍታት በተጨማሪ ከሀገር የከተማ ግብርናን ሁሉም የሚተገብረው ባህል በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን የሚጨምር ነው ብለዋል።

በተያዘው አመትም የከተማ አስተዳደሩ ክፍት በሆኑ አነስተኛም ይሁኑ ሰፋፊ መሬቶች ላይ ለግብርና ይውላሉ ብለዋል።

ከከተማ ግብርና ጋር በተያያዘ ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፉና የስራ እድል እንዲያገኙ ዝግጅት ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.