Fana: At a Speed of Life!

ለኮሮናቫይረስ ክትባት ማፈላለግ ስራ የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት የማፈላለግ ስራውን ለማፋጠን የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ።

ከ7 እስከ 8 የሚሆኑ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተመርጠው እየተሰራባቸው መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቅዋል።

የክትባቶቹን አይነት ይፋ ያላደረጉት ዶክተር ቴድሮስ፥ ከ100 በላይ የክትባት አይተነቶች እንደቀረቡና ከእነዚህም ውስጥ የተሻሉ እና ውጤታማ ይሆናሉ ተብሎ የታመነባቸው ከ7 እስከ 8 የሚሆኑ ተመርጠው እየተሰራባቸው ነው ብለዋል።

ክትባት የማበልፀግ ስራው ላይም ከ400 በላይ ተመራማሪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

ቀደም ብሎም ለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) መከላከያ ክትባት የመስራት ስራው ከ12 እስከ 18 ወራትን ሊወስድ እንደሚችልም ዶክተር ቴድሮስ መግለፃቸው ይታወሳል።

ሆኖም ግን የለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ 19) መከላከያ ክትባት ስራው በተፋጠነ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ዶክተር ቴድሮስ፥ የክትባት ስራው ባሳለፍነው ሳምንት በ40 ሀገራት፣ ኩባንያዎች እና ባክኖች የ8 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንደተደረገም አስታውሰዋል።

8 ቢሊየን ዶላር ለክትባት ስራው በቂ አይደለም ያሉት ዶክተር ቴድሮስ፥ የዓለም ሀገራት እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያደርጉትን ድጋፍ በተፋጠነ መልኩ ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ምንጭ፦ aljazeera.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.