Fana: At a Speed of Life!

ለውጡ የመሀል ተዋናይነትና የዳር ተመልካችነትን አስቀርቷል -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ ከሴት አደረጃጀቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ ተገኝተዋል።

በምክክር መድረኩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለውጡ ባስገኛቸው ስኬቶች ሁሉ የሴቶች ሚና ላቅ ያለ መሆኑን አውስተዋል፡፡

የሴቶች እና የሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች የፍትሀዊ ተጠቃሚነት ጥያቂ ለለውጡ መምጣት አንደኛው ገፊ ምክንያት መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ከንቲባዋ ሴቶችን ያገለለ ለውጥ ግማሽ ለውጥ ስለሆነ ውዝፍ የሆኑ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ስራዎችን በማጥራት ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የከተማ አስተዳደሩ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባለፈው አመት ያከናወነው የተማሪ ምገባ ፕሮግራም በዚህ አመትም ጫማና ቦርሳ ጭምር ለማሟላት ታቅዶ እየተሰራ በመሆኑ የሴቶችን ጫና እንደሚያቃልለው የገለፁት ወይዘሮ አዳነች ሴትን ማስተማር ቤተሰብን ማስተማር በመሆኑ ለዚህም ትኩረት እንደሚሰጠው መናገራቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ አለሙ የኢትዮጵያ እናቶች ጥያቄ የሚመለሰውና እረፍት የሚያገኙት ሁለንተናዊ ብልፅግና ሲረጋገጥ በመሆኑ የሴት አደረጃጀቶች አገር በቀል ዕውቀቶችንና ልምዶችን በማጎልበት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በህዳሴ ግድቡ ላይ የተሰራው ታሪክ፣ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚወሰዱ እርምጃዎችና በትግራይ ክልል በአጭር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ህግን የማስከበር እርምጃ ሴቶቹ በለውጡ ላይ ያላቸውን እምነት የበለጠ እንዳጠናከረው እንደሚቀጥሉ  በውይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.