Fana: At a Speed of Life!

ለዘመቻው ደጀን ከመሆን ባለፈ በልማቱ ጠንክረን እየሰራን ነው – የጊኒር ወረዳ አርሶ አደሮች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ የተመራ ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት ኃላፊዎች ልዑክ በምስራቅ ባሌ የተሓሻሉ የግብርና አሰራሮችን ተግባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮችን ማሳ ጎብኝቷል፡፡

በመስክ ምልከታው በክልሉ በ2013/14 የምርት ዘመን ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ የሰብል መልማቱም ተመልክቷል፡፡

አርሶ አደሮች አገራችን በአሁኑ ወቅት እያደረገች የምትገኘው የህልውና ዘመቻ በስኬት እንዲጠናቀቅ በግንባር እየተዋደቀ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ስንቅ ማዘጋጀትን ጨምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ደጀን ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

የህልውና ዘመቻውን ከመደገፍ በተጓዳኝ በተለይ በጦርነቱ ምክንያት ከእርሻ ስራ ውጭ የሆኑ የአገራችን አርሶ አደሮች ለመደገፍ ጠንክረን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

በአንድ እጃችን ልማታችንን በማካሄድ በአንድ እጃችን ደግሞ አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ እየተደረገ የሚገኘው ዘመቻ ባጠረ ጊዜ በስኬት እንዲጠናቀቅ በቁጭት እየሰራን ነውም ብለዋል አርሶ አደሮቹ።

የምስራቅ ባሌ ዞን የእርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሹክሪ ጣሃ በበኩላቸው፥ በዞኑ በ2013/14 የምርት ወቅት በተለያዩ የሰብል ዘሮች ከለማው 124 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ 41 በመቶ የሚሆነው በኩታ ገጠም ክላስተር የለማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም ቃሲም በዞኑ የህልውና ዘመቻው በስኬት እንዲጠናቀቅ አርሶ አደሩን ጨምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የህልውና ዘመቻውን እየደገፉ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተለይ አርሶ አደሩ በጦርነቱ ምክንያት ሊቀንስ የምችለውን ምርት ለማካካስ ጭምር እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ አበራ ወርቁ እንዳሉት በክልሉ በ2013/14 የምርት ወቅት በተለያየ የሰብል ከለማው ከ6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት 50 በመቶ የሚጠጋው በኩታ ገጠም ክላስተር የለማ ነው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.