Fana: At a Speed of Life!

ለዘማች ልጆች ነጻ የትምህርት እድል ሊሰጥ ነዉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በጎንደር ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ለዘማች ቤተሰብ ልጆች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መወሰናቸውን አስታወቁ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የከፈተውን ጦርነት ለመመከት በግንባር የዘመቱ ጀግኖችን ልጆች ማስተማር በሚቻልበት ዙሪያ በትምህርት መስክ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ ባለሀብቶች ጋር መክሯል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ ባለሀብቶች ሀገርን ለማፍረስ የመጣውን ጠላት ለመዋጋት ቤተሰቦቻቸውን ጥለው የዘመቱ የቁርጥ ቀን ጀግኖችን ልጆች ማስተማር ኩራት መሆኑን ገልፀዋል።
ከውይይቱ በኃላም ባለሀብቶቹ ለዘማች ልጆች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት መወስናቸው ተገልጿል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ አግማስ በበኩላቸው÷ አሸባሪው ህውሓት የፈፀመውን ወረራ መሰረት አድርጎ በግንባር የዘመቱ ጀግኖች ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ናቸው ብለዋል።
በግንባር ያልዘመተውም ደጀን በመሆን የበኩሉን መወጣት አለበት ያሉት ምክትል ከንቲባው÷ በትምህርት ዘርፉ የተሰማሩ የከተማዋ ባለሀብቶችም የዘማች ቤተሰቦችን ለማስተማር መፍቀዳቸው የትግሉ አካል መሆኑን አስረድተዋል።
486 የዘማች ቤተሰቦች የተለዩ መሆኑን የተናገሩት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ አክሊሉ ወንድምአገኝ÷ በጎንደር ከተማ የሚሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ከቅድመ መደበኛ እስከ ዩንቨርሲቲ ባለው ደረጃ ነው የዘማች ቤተሰቦችን ለማስተማር የወሰኑት ብለዋል።
ስንታየሁ አራጌ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People Reached
11
Engagements
Boost Post
11
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.