Fana: At a Speed of Life!

ለዩጋንዳ የሚዲያ ተቋማት አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች እና የማህበረሰብ አንቂዎች የምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩጋንዳ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ለዩጋንዳ የሚዲያ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮች እና የማህበረሰብ አንቂዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ባለፈው አንድ አመት ላቀረቡት አዎንታዊ ዘገባ የምስጋና ፕሮግራም አካሄዷል።
 
በዩጋንዳ የኢፌዴሪ አምባሳደር ዓለምፀሐይ መሰረት አንዳንድ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በአገራችን ላይ እያሰራጩት ባለው ሀሰተኛ መረጃ ሳይጠለፉ እውነቱን ፈልጎ በመዘገብ ላሳዩት ሙያዊ ስነ-ምግባር በእጅጉ አድንቀዋል።
 
በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአባይን ወንዝ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት፣ ግድቡ የምስራቅ አፍሪካ አገራትን ከማስተሳሰር አንጻር ያለውን ፋይዳ፣ የሶስቱ አገራት ድርድር በአፍሪካ ህብረት መቀጠል እንዳለበት በርካቶች አጉልታችሁ ፅፈችኋል፣ ተናግራችኋል ለዚህም ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
 
በአገራችን በሰሜኑ ክፍል የተከሰተውን ጦርነት በተመለከተ በዪጋንዳ በማህበረሰብ አንቂዎች በትዊተር ገጻቸው እንዲሁም የኦንላይን ሚዲያዎች እውነቱን ከማስገንዘብ እና ትክክለኛ መልክት ቀርፆ ከማስተላለፍ አንጻር ተሳትፎው ቀላል አለመሆኑን ጠቅሰዋል።
 
ሌሎችም የሚዲያ ተቋም እና ጋዜጠኞቹ የእነዚህን አርአያ በመከተል የአገራችንን ሁኔታ በሚመለከት ሙያዊ ስነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ገለልተኛና ትክክለኛ ዘገባዎችን እንዲሰሩ አሳስበዋል።
 
ዩጋንዳውያን ዬቴለቪዥን ሾው አዘጋጆች እና መሪዎች በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ታሪክ ምልክት፣ፓን አፍሪካኒዝምን ያቀጣጠለች አገር ብቻ ሳትሆን የአፍሪካ የወደፊት እድል ላይ ያላት ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያን ጉዳይ አፍሪካውያን በንቃት እንደሚከታተሉት ገልጸዋል።
አፍሪካ የራሷ የሆነ የሚዲያ ተቋም የሌላት በመሆኑ አፍሪካውያን የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሰለባ ሆነናልም ነው ያሉት።
አያይዘውም የዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት በሚሰጡን አጀንዳ ላይ የተመሰረተ ህይወት እንድንኖር አድርገውናል፣ እነሱም ስለ አፍሪካ የሚያስተላልፉት ዘገባ በአብዛኛው አፍራሽ የሆነ፣ ነባራዊ ሁኔታንና አፍሪካዊ ማንነትን ያላገናዘበ በመሆኑ አፍሪካ የራሷ የሆነ ገፅታዋን ሊገነቡ የሚችል ሚዲያ ተቋም ያስፈልጋታል ብለዋል።
በእለቱ ዋና ዋና የሚዲያ ተቋማት ከተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች፣ ዋና አዘጋጆች፣ ዘጋቢዎች፣ የማህበረሰብ አንቂዎች በፕሮግራሙ ላይ መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.