Fana: At a Speed of Life!

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልል የአማራ ክልል መንግስት ድጋፍ አይለየውም – ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በይፋ በአዲስ ለተመሠረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ክልልን ለማጠናከር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ÷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ 11ኛ ክልል ሆኖ በይፋ በመመስረቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአገራችን ህዝብ ህወሓት መራሹን ስርዓት ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ በጋራ በተነሳበት ወቅት÷ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ 11ኛ ክልል ሆኖ መመስረቱ ልዩ እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት የኢትዮጵያ ህዝብ ለአምሳ ዓመታት ያህል በአንድ ቡድን ፍላጎት ብቻ ከሚደፈጠጥበት ስርዓት አላቆ በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ እውነተኛ ፌደራላዊ እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ ነውም ብለዋል ዶክተር ይልቃል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት÷ አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት እና ህዝብ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስታትና ህዝቦች ሁሉ በህዝቦች መካከል ያለውን ኢትዮጵያዊ አንድነት ለማስጠበቅ እና የአገርን ሉአላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው የህልውና ትግል ሒደት የማይተካ ሚናውን እንደሚወጣ የጸና እምነት አለኝ ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.