Fana: At a Speed of Life!

ለድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ስጋት እየሆነ የመጣው የጅብ መንጋ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለድሬዳዋ ከተማ የገንደ ሮቃ አካባቢ ነዋሪዎች የጅብ መንጋ ስጋት እያሳደረባቸው መምጣቱ ተሰምቷል፡፡

ከቀድሞው ምድር ባቡር ድርጅት፣ ከጉምሩክና ከምስራቅ አየር ኃይል በተለምዶ ሰባተኛ ከሚባለው የጦር ካምፕ የሚዋሰነው ገንደ ሮቃ የሚባለው መንደር ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥሻ እየተዋጠ በመምጣቱ የጅብ መንጋ የሚርመሰመስበት ስፍራ መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

በአካባቢው የጅብ መንጋ ከጎሬው እየወጣ ነዋሪዎችን እንደሚተናኮል ነው የተገለፀው፡፡

በአንድ ወር ገዜ ውስጥ ብቻም ለአራተኛ ጊዜ መተናኮሉንም ነው የነዋሪዎቹ ሚናገሩት።

ከምድር ባቡር ድርጅት የፍሳሽ ቱቦዎች፣ ከሰባተኛ ጦር ካምፕና ከጉምሩክ የሚጣሉ ተረፈ ምርቶች የጅብ መንጋው በአካባቢው እንዲበራከት ምክንያት መሆኑም ተገልጿል።

ምግብ ፍለጋ የሚወጣው የጅብ መንጋ ባለፈው ቅዳሜ ለአንድ 3 ዓመት ህፃን ህልፈት ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው፡፡

መሰል ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይከሰትም መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግለት ነዋሪዎቹ መጠየቃቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.