Fana: At a Speed of Life!

ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጃዋር መሃመድ አራት ሲም ካርዶችን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሊያቀብል ሲል ተይዟል የተባለው ተጠርጣሪ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
ተጠርጣሪው ግለሰብ ሃምዛ ጀማል መሃመድ ይባላል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተጠርጣሪው ታህሳስ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. 1ኛው ሲም ካርድ በኦ ኤም ኤን ድርጅት ስም ማውጣቱን ጠቅሶ ሶስቱ ሲም ካርዶች ደግሞ በግለሰብ ስም የወጡ መሆናቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም መጣራቱን ገልጿል፡፡
ግለሰቡ እነዚህን ሲም ካርዶች በመያዝ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመሄድ ጃዋር መሃመድን ልጠይቅ ነው በሚል ገብቶ ሲም ካርዶችን ለጃዋር መሃመድ ሊያቀብል ሲል መያዙንም አብራርቷል፡፡
ተጠርጣሪው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ ጉዳዩ እየታየ ነው፡፡
ተጠርጣሪው ጃዋርን ለመጠየቅ መሄዱንና ስልኩ በመበላሸቱ አራት ሲም ካርድ መያዙን በመጥቀስ በአቃቂ ቃሊቲ ከአንድ ሳምንት በላይ መታሰሩን በማንሳትም የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ጠይቋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም 1ኛው ሲም ካርድ አቶ ጃዋር መሃመድ ሲራጅ የሚያስተዳድሩት የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦ ኤም ኤን) ነው፤ ግለሰቡ እንደሚሉት ሳይሆን ሲም ካርዶችን ለማቀበል ሲሉ በማረሚያ ቤቱ አባላት ነው የተያዙት ብሏል፡፡
በተጨማሪም ምርመራ መጀመሩን ጠቅሶ ከተጠርጣሪው ጀርባ ያሉ ግብረ አበሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑንም ለችሎቱ አስረድቷል፡፡
ፍርድ ቤትም በሁለተኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለመርማሪ ፖሊስ 14 ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዶለታል፡፡
በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Front page – Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C
fanabc.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.