Fana: At a Speed of Life!

ለ1 ሚሊየን ወደ አገር ቤት ዘመቻ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 1 ሚሊየን ዳያስፖራ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የቅድመ ዝግጅት ስራ እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው የዳያስፖራ ጉዳዮችን እንዲያስተባብር በማቋቋሚያ ደንቡ ሃላፊነት እንደተሰጠው የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡

ዳያስፖራው ካለበት አገር ጀምሮ ኢትዮጵያ እስከሚገባ ድረስ እንዲሁም በቆይታው ወቅት ስለሚኖሩ ሁነቶችና መከናወን ስላለባቸው ጉዳዮች የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ዳያስፖራው በስፋት በሚኖርባቸው አገራት ባሉ ኤምባሲዎችና በአገር ቤት ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመስራት የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ ለሚወዷት ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ዳያስፖራው ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ በስፋት ወደ አገር ቤት በመምጣት በኢትዮጵያ ላይ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመፍጠር በመንቀሳቀስ ላይ ላሉ አካላት ግልጽ መልዕክቱን በድጋሚ እንዲያስተላልፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.