Fana: At a Speed of Life!

ለ11 ሆስፒታሎች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ሆስፒታሎች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በጦርነቱ ምክንያት ውድመት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም ሰፊ ርብርብ ቢደረግም እስካሁን በታሰበው ልክ ችግሩን መፍታት አልተቻለም ብለዋል።

ከዚህ አንጻርም የአጋር አካላት እገዛ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

በኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም ዛሬ የተደረገው ድጋፍ÷ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ሆስፒታሎች ወደ ቀደመ ሥራቸው ለመመለስ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋልም ነው ያሉት።

የኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ÷ የተደረገው ድጋፍ ክፍተቶችን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

መሳሪያዎቹ አገልግሎት ሲጀምሩ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ አገልግሎት መስጠት ያስቻላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ የኮሪያ መንግስትና ኤግዚም ባንክ ለኮቪድ – 19 ምርመራ የሚያገለግል የላቦራቶሪ መመርመሪያ ኪት ድጋፍ አበርክተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.