Fana: At a Speed of Life!

ለ12 ዓመታት በተመሳሳይ ቁጥሮች ሲጫወት የቆየው የጃክፖት ሎተሪ  አሸናፊ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለ12 ዓመታት በተመሳሳይ ቁጥሮች ሲጫወት የቆየው ሰው የጃክፖት ሎተሪ አሸናፊ  መሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል።

አሜሪካዊው ዳን ዳምፍ ተመሳሳይ የሎተሪ ቁጥሮችን  በመጠቀም ከ 10 ዓመታት በላይ ሲጫወት ቆይቶ የ 50 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆኗል።

የጄፈርሰን ከተማው ዳን ዳምፍ በአውሮፓውያኑ በ 2008 ጀምሮ ላለፉት 12 ዓመታት ተመሳሳይ 10 ቁጥሮችን በመጠቀም  ሲጫወት መቆየቱን ተናግሯል።

ባለእድለኛው  ሎተሪ ሲያሸንፍ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልጾ÷ከሁለት ዓመት በፊት 19 ሺህ ዶላር ማሸነፉን  አስታውሷል።

የአካባቢው የሎተሪ  መስሪያ ቤት ባለሥልጣናትም  በተመሳሳይ ቁጥር እንደሚጫወት ነግሯቸው እንደነበር ተናግረው ÷ ጽናቱ ከፍሎታል ብለዋል ።

ዳን ዳምፍ በደረሰው ገንዘብም ያሉበትን እዳ ከከፈለ በኋላ አዳዲስ የእንጨት ሥራ መሣሪያዎችን ለመግዛት ማቀዱን ተናግሯል።

ምንጭ ፡- upi.com

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.