Fana: At a Speed of Life!

ሊከፋፍሉን የመጡ እኩይ ድምጾችን በጋራ እናሸንፋቸዋለን- ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊከፋፍሉን የመጡ እኩይ ድምፆችን በጋራ እናሸንፋለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷በአንድነት በፅናት እንቆማለን፣ኢትዮጵያን ማሸነፍ ፈፅሞ አይቻልም ብለዋል፡፡
በተፈጥሮ ሃብቷ እና ፈጣሪ በለገሳት ፀጋ አይናቸው የቀላ ሃይሎች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ ገጥመው የብተናና የመከፋፈል ድምፆችን እያስተጋቡ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡
 
በብዙ ዋጋ እና መስዋዕትነት እኛ እጅ የደረሰችን ኢትዮጵያ አሳልፈን አንሰጥም ፣በአንድነትና በፅናት እንቆማለን፣ ትብብራችን አሸናፊ ነው ብለዋል፡፡
 
እነዚህ የብተና ድምፆች ይሰላሉ፤ በአገሬ ላይ የተከፈቱ አንደበቶችን ይዘጋሉ፣ኢትዮጵያችን ታሸንፋለችም ሲሉ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.