Fana: At a Speed of Life!

ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ሰራዊቱ ድል የተጎናፀፈባቸው ሥፍራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጠና የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ ሃይሎች ተደምስሰው ሰራዊታችን ድል የተጎናፀፈባቸው ሥፍራዎችን ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ጎበኙ ።
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ፣ የፌዴራል ፖሊስ ፣ የክልል ልዩ ሐይል አባላት እና የመተከል ዞን የሚኒሻ አባላት በጋራ ክንዳቸው ጀብድ በመፈፀማቸው የሕዳሴው ግድብ ያለአንዳች የፀጥታ እንከን እየተከናወነ እንደሚገኝ በመዘዋወር የምድር ሃይል ዋና አዛዥ እና የመተከል ኮማንድ ፖስት የተቀናጀው ግብረ ሃይል አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ አረጋግጠዋል።
ጄኔራል መኮንኑ በጉብኝታቸው ወቅት እንዳሉት ፥ አሸባሪውን እና ቅጥረኛ የውክልና ተላላኪ ሃይሎችን በቅርቡ ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርገን በማጥፋት የሕዳሴውን ግድብ ብርሀን እንመለከታለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.