Fana: At a Speed of Life!

ልማት ባንክ አሸባሪው ህወሓት ያደረሰውን ውድመት ለማካካስ የግብርና መሳሪያዎች በሊዝ ሊያቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች ያደረሰውን ውድመት ለማካካስ በቀጣዮቹ የምርት ወቅቶች የግብርና መሳሪያዎች በሊዝ ለማቅረብ የፋይናንስ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት÷ የሽብር ቡድኑ ባንኩ በሚደግፋቸው ፕሮጀክቶች ላይ ያደረሰውን ተፅዕኖና ውድመት የሚያጠና ቡድን አሰማርቷል።
በርካቶቹ ባንኩ የሚደግፋቸው ፕሮጀክቶች በትግራይ ክልል የሚገኙ መሆናቸውንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ከአሸባሪው ህወሓት ነፃ በወጡ አካባቢዎች የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ባንኩ በአሸባሪ ቡድኑ የደረሰውን ውድመት ለማካካስ በቀጣዮቹ የምርት ወቅቶች የግብርና መሳሪያዎችን በሊዝ ለማቅረብ መዘጋጀቱንም ዶ/ር ዮሐንስ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ በርካታ ዘርፎችን ሲደግፍ የነበረና ዕድሜ ጠገብ ቢሆንም÷ የአሸባሪ ቡድኑ አባላት ስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ ሲከተሉት በነበረው ያልተገባ አካሄድ አሰራሩ ጤናማ ሂደትን ያልተከተለ እንደነበረም ነው የገለጹት።
ባንኩ ያልተገቡ አሰራሮችን ለማስወገድ ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች የተበላሸ ብድርን ከነበረበት 35 በመቶ ወደ 26 በመቶ ማውረድ መቻሉንም አብራርተዋል ኃላፊው፡፡
ባንኩ ለተለያዩ ኢንተርፕራይዞች የፕሮጀክትና ሊዝ ፋይናንሲንግ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.