Fana: At a Speed of Life!

ልዩ ጣዕም ያላቸው የኢትዮጵያ ቡናዎች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጣዕማቸውና ጥራታቸው ሊቀንስ ይችላል-ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ልዩ ጣዕም ያለው የኢትዮጵያ ቡና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ጣዕሙ ሊቀንስ እና ሊቀየር እንደሚችል አንድ ዓለም አቀፍ ጥናት አመለከተ።

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ወደ ፊት ኢትዮጵያ የተለየ ጣዕም ካለው ቡናዋ ይልቅ ጣዕሙ የማይወደደው ቡና ልታመርት ትችላለች ብሏል።

ፖትስዳም ኢንስቲትዩት ለአየር ንብረት ተፅዕኖ ጥናት በኢትዮጵያ የቡና ምርት ላይ የአየር ንብረት ለውጥ የሚኖረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናት አካሂዷል።

የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ የቡና ምርት ላይ የሚቃረኑ ተፅዕኖዎች እንዳሉት የሚገልጹት የጥናት ቡድኑ አባል አቤል ቼሙራ አማካይ ጣዕም ያለው የኢትዮጵያ ቡና መጠን እስከ ፈረንጆቹ 2090 ድረስ እድገት ሊያሳይ እንደሚችል ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የአየር ንብረት ለውጥ በዚህ ከቀጠለ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የኢትዮጵያ ቡናዎች ጥራታቸው እንደሚቀንስ የጥናት ቡድኑ አባል አቤል ቼሙራ ተናግረዋል።

ይህ ስጋት ለቡና አፍቃሪዎች ብቻ ሳይሆን በአካባቢዎቹ ከቡና ሀብት ለሚፈጥሩትም ነው ብለዋል።

ተመራማሪዎቹ በተለያዩ ቢሆኑዎች 19 የአየር ንብረት ለውጥ አይነቶች ልዩ ጣዕም ባላቸው የኢትዮጵያ ቡናዎች ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖዎች ገምግመዋል።

ከዚህም ውስጥ የሙቀት መጨመር፣ ዓመታዊ የዝናብ መጠን እና ወቅታዊነት እንደሚጠቀሱ ነው ኢስያ ኒውስ ኢንተርናሽናል በዘገባው  ላይ ያሰፈረው።

በዚህ ጥናት ቢሆኑዎች መሰረት በተለይ የይርጋጨፌ ቡና በ21ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ልዩ ጣዕሙን ከፍ ባለመጠን ሊያጣ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.