Fana: At a Speed of Life!

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከስደት ለተመለሱ 140 ዜጎች የስራ እድል አመቻቸ 

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ከስደት ለተመለሱ 140 ዜጎች የሥራ እድል ማመቻቸቱን አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲው ከአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር የስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዲያገኙ እያከናወነ ያለውን ሥራ እየተገመገመ ነው።

በዩኒቨርሲቲው የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋም አስተባባሪ ዶክተር  ከተማ በቀለ እንደገለጹት÷ ከአይኦኤም ጋር በዞኑ ከስደት የተመለሱ ዜጎችን ወደ ስራ ለማስገባትየተቀናጀ ስራ ሲያከናውኑ ቆይተዋል።

ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር በተከናወነው ሥራ በዞኑ 12 ወረዳዎች 140 ተመላሽ ዜጎች የማሀበራዊ፣ ስነ ልቦናዊና የንግድ ክህሎት ስልጠና በመስጠት የሥራ እድል እንደተመቻቸላቸው ተናግረዋል።

ንግድ፣ እንስሳት እርባታና ማደለብ  እንዲሁም ኤሌክትሮክስ ጥገና  ከተመቻቸላቸው የሥራ እድል ውስጥ እንደሚገኙበት ዶክተር ከተማ ጠቅሰው÷ በዚህም ከጠባቂነት በመላቀቅ ራሳቸውን እየቻሉ መሆኑን አስረድተዋል።

ለዚህም አይኦኤም 9 ሚሊየን 400 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.