Fana: At a Speed of Life!

መቐለን ጨምሮ የብር ቅያሪ ከተጀመረ 14 ቀናት ባለፋቸው የትግራይ ከተሞች አገልግሎቱ መጠናቀቁ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በሕግ የማስከበር ዘመቻ ምክንያት የተቋረጠው የብር ቅያሪ ሥራ ከታህሣሥ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ቀን ታራዝሞ እንደነበር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውሷል።

ሆኖም የተራዘመውን ጊዜ አቆጣጠር በተመለከተ ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ተከትሎ

በጉዳዩ ዙሪያ ግልፅነትን መፍጠሩ አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

በእስካሁኑ የክልሉ የብር ቅያሪ አፈፃፀም ግምገማ መሠረት የተራዘመው ጊዜ ለእያንዳንዱ የባንክ

ቅርንጫፍ የተሰጠ መሆኑ ቀርቶ ለእያንዳንዱ የክልሉ ከተማ እንዲሆን ተደርጓል ተብሏል፡፡

በመሆነም ከዛሬ 17 ቀን ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ አንድ ከተማ ቀድሞ አገልግሎት የሚጀምር የባንክ ቅርንጫፍ ሲኖር የዚያ ከተማ የተራዘመው የብር ቅያሪ ጊዜ የሚቆጠረው ይኸው የባንክ ቅርንጫፍ በከተማው ቀድሞ ሥራ ከጀመረበት ቀን አንስቶ ለ14 ቀናት ብቻ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

ዘግይተው ሥራ የሚጀምሩ ሌሎች የባንክ ቅርንጫፎች በከተማው አሮጌ ብር መቀየር የሚችሉት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ነው ብሏል ባንኩ።

በመሆኑም መቐለን ጨምሮ የብር ቅያሪ ከተጀመረ 14 ቀናት ባለፋቸው የትግራይ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው የብር ቅያሪ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጧል፡፡

ስለዚህ በየትኛውም የክልሉ ከተማ የሚገኝ ህብረተሰብ ይህን ተገንዝቦ በተጠቀሱት 14 ቀናት ብቻ በከተማው ወደሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች በመቅረብ የአሮጌ ብር ቅያሪ አገልግሎት እንዲያገኝ ባንኩ አሳስቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.