Fana: At a Speed of Life!

መንትያ ዶክተሮቹ በጂማ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለቱ መንትያ ወንድማማች ዶክተሮች ከ 25 አመት በፊት በነቀምት ከተማ ነው የተወለዱት፡፡
ጅማ ዩኒቨርሲቲ መስከረም 8፣ 2014 ካስመረቃቸው የህክምና ተማሪዎች መካከል እነዚህ መንትዮች ይገኙበታል።
ነጋሳ ብራቱ እና ነገሪ ብራቱ ይባላሉ።
ከፊት ገጻቸው መመሳሰል ባሻገር÷ በትምህርት ቤት ቆይታቸዉ ያስመዘገቡት ዉጤትም ተመሳሳይ መሆኑ ግርምትን ፈጥሯል፡፡
መንትያ ሆነው አንድ ትምህርት ቤት መማር እድልም ፈተናም መሆኑን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል፡፡
እድሉ ስሜትን እኩል መካፈል ሲሆን÷ ፈተናው ደግሞ በትምህርት ቆይታችን ጥያቄ ይበዛብን ነበር ብለዋል።
ወደ ፊት እነሱም መንትያ ልጆችን መውለድ እንፈልጋለን ሲሉ መንትያ ዶክትሮቹ ምኞታቸዉን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.