Fana: At a Speed of Life!

መንትዮቹ በተመሳሳይ ከፍተኛ ውጤት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንትዮቹ በተመሳሳይ የትምህርት ክፍለ እኩል 3 ነጥብ 59 ውጤት በማምጣት በልዩ ሽልማት ጭምር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመረቁ ።
የተወለዱት አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነው፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መስኮች ዛሬ ካስመረቃቸዉ 6 ሺህ 793 ተማሪዎች መካከል የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መንቲዮች ምርቃቱን ልዩ አድርገውታል።
ፍላጎታቸው ተመሳሳይ የትምህርት ክፍለ በመከታተል 3 ነጥብ 59 እኩል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በልዩ ሽልማት ጭምር ነዉየተመረቁት።
የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ ማኔጅምንት ትምህርት ክፍል ተማሪዎቹ በእምነት እና በአምላክ ጌታነህ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በመመሳሰላቸው ተማሪዎችንን እና መምህራንን ግር የሚያሰኙት መንትዮቹ ተመሳሳይ ትምህርት መስክና በተመሳሳይ ውጤት በሽልማት አጠናቀዋል።
ከፋና ሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ተማሪዎቹ በተለይ ሴቶች ተስፋ ባለመቁረጥ በጥንካሬ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገብነው በጋራ ጠንከረን በማጥናታችን ነው ያሉት በእምነት እና በአምላክ በተመረቁበት ዘርፍ የተሻለ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በጌታቸው  ሙለታ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.