Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በትግራይ ክልል ለ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ድጋፍ መሰራጨቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል እስካሁን ለ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ድጋፍ መሰራጨቱን አስታወቀ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም በክልሉ ከሚገኙ 36 ወረዳዎች ውስጥ በ34 ወረዳዎች ሰብአዊ ድጋፍ መቅረቡን ጠቅሶ፥ በዚህም እስካሁን 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ነው ያለው፡፡

ከቀረበው ሰብአዊ ድጋፍ ውስጥ 70 በመቶው ድጋፍ በመንግስት ሲሸፈን 30 በመቶውን ደግሞ ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች መሸፈናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በ10 ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች አማካኝነት ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ እየቀረበ ሲሆን ለዚህም ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉ 10 ጣቢያዎች ተቋቁመዋል ነው የተባለው፡፡

የሰብዓዊ ድጋፍ ጥረቱ እየተካሄደ የሚገኘው አጋር ሃገራት እና ኤጀንሲዎችን ጨምሮ በዘርፉ ባለሙያዎች የጋራ ጥናት ላይ ተመስርቶ መሆኑንም ነው ጽህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም እስካሁን 135 የሚደርሱ የተለያዩ ሃገራት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ፈቃድ በመውሰድ እየንተቀሳቀሱ ይገኛሉም ብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተቋቋመው አስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ኮሚቴ ስር በመሆን 29 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙም አብራርቷል፡፡

መገናኛ ብዙኀንን በተመለከተ ለ7 ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ማለትም ኤ ኤፍ ፒ፣ አልጀዚራ፣ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ፍራንስ 24፣ ሬውተርስ፣ ቢቢሲና ፋይናንሺያል ታይምስ በክልሉ እንዲንቀሳቀሱ ፍቃድ መስጠቱንም አስታውቋል፡፡

መንግስት ከህግ ማስከበሩ ጋር ተያይዞ በግልጽና በድብቅ የሚሰራጨውን ሀሰተኛ መረጃ እንደሚገነዘብም ነው መግለጫው ያነሳው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በውጭ የሚገኙና በጥፋት ኃይሎች በገንዘብ የሚደገፉ ቅጥረኛ ሚዲያዎች ማህበራዊ ትስስር ገጾችንና ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም መሬት ላይ ያልተፈጸሙ የተጋነኑ መረጃዎችን እያሰራጩ እንደሚገኙም አውስቷል፡፡

ትግራይ ክልልን በተመለከተ ድብቅ አጀንዳ ባነገቡና የተለየ የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ኃይሎች የሚሰራጨው የተሳሳተ ዘገባ እንዳሳሰበውም አንስቷል፡፡

ከመንግስት በክልሉ ለሚገኙ ዜጎች ደህንነትና ሰላም ለማረጋገጥ የገባውን ቃል እንደሚያከብር ጠቅሶ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ ያነገቡ ኃይሎች ከሚያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ እንዲጠበቁም አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.