Fana: At a Speed of Life!

መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡

በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫውም በኢትየጵያ እና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር መካከል የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘቡን አንስቷል፡

ድርጊቱ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የተፈጸመው በአሸባሪው የህወሓት አባላት የሚደገፈው የሱዳን መደበኛ ጦር ሰራዊት የኢትዮጰያን መሬት ከወረረ በኋላ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን ጦር እና በአካባቢው ባለው ሚሊሻ መካከል በተፈጠረ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኑን የገለፀ ሲሆን÷ በቅርቡም በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ አስገንዝቧል፡፡

የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት ፀብ ጫሪ ድርጊት የፈፀመው ወገን የሱዳን ጦር ሆኖ ሳለ በሁኔታው ኢትዮጵያን ተጠያቂ ለማድረግ የሚሞከርን የትኛውንም ድርጊት መንግስት እንደማይቀበል አስታውቋል።

የሱዳን መንግስት ሁነቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶች በመቆጠብ የተፈጠረውን ድርጊት ሊያርግቡ የሚችሉ እርምጃዎችን እንደሚወስድ የኢትዮጵያ መንግስት ተስፋ እንደሚያደርግም መግለጫው አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የተፈጸመው ድርጊት በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ስር የሰደደ ግንኙነት ለማፍረስ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን ገልፆ፥ ኢትዮጵያ የተያያዘችውን የሰላምና የዕድገት ጎዳና ለማደናቀፍ ያለመ መሆኑንም አስረድቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም በሀለቱ ሀገራት መካከል ያሉ ማናቸውንም ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አቋም እንዳለውም አስገንዝቧል፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.